የኦሮሚያ ክልል የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የተከናወኑ የዕቅድ አፈፃፀም ተግባራትን የሚገመግም መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የክልሉ መንግስት የልማት ስራዎችን በብዛት፣ በጥራት እና በፍጥነት ማከናወን የሚያስችል ዕቅድ ነድፎ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የግምገማ መድረክ ዕቅዱን ለማሳካት የሚደረገው ድጋፍ እና ክትትል ይፈተሻል ተብሏል።
በመድረኩ የከተማ ልማት ክላስተር፣ የገጠር ልማት ክላስተር እና ማህበራዊ ልማት ክላስተር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
ግምገማው ሲጠናቀቅ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡