Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ95 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የበጋ ወቅት በመደበኛ መስኖ ከ93 ሺህ እንዲሁም በበጋ ስንዴ ልማት ከ2 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የግብርና ዘርፍ የ6 ወራት አፈጻጸም የምክክር መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት፥ በሁለት ዙር የመስኖ ልማት 147 ሺህ ሄክታር መሬትን በመስኖ ለማልማት እየተሠራ ነው፡፡

በዚህም መሬቱን ፍራፍሬን ጨምሮ በበጋ ስንዴና በሌሎች ሰብሎች በመሸፈን 33 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከዚህ ጥቅል እቅድ ውስጥም 136 ሺህ ሄክታር መደበኛ መስኖ፤ 11ሺህ ሄክታር የበጋ ስንዴ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱም 434 ሺህ ኩንታል ምርት ለማግኘት ግብ መቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.