Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የጀርመን ግንኙነትን የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የጀርመን ግንኙነትን የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ሐሳባቸውን ያጋሩት በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር እና የሊቢያ ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት ክርስቲያን ባክ(ዶ/ር) ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

አምባሳደር ምሥጋኑ ÷ ኢትዮጵያና ጀርመን በልማት ድጋፍ፣ በቴክኒካዊ ትብብር እንዲሁም በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡

ስለ ፕሪቶሪያው የሠላም ሥምምነት የአፈፃፀም ሂደት ብሎም በኢትዮጵያ ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ እና የሽግግር ፍትኅን ዕውን ለማድረግ እየተደረገ ስላለው ዝግጅት ገለጻ እንዳደረጉም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በጋራ ጥቅማቸው ላይ የተመሠረተ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይም ሐሳብ መለዋወጣቸው ነው የተጠቆመው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.