ስፓርት

በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ጋምቢያን 3 ለ 0 አሸነፈች

By Mikias Ayele

January 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሴኔጋል ጋምቢያን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡

የሴኔጋልን የማሸነፊያ ግቦች ፔፔ ጉዮ እና ላሚን ካማራ አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው የጋምቢያው ተከላካይ ኢብራሂማ አዳምስ በፈፀመው ያልተገባ ባህሪ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ መርሐ ግብር ምሽት መካሄዱን ሲቀጥል ምሽት 2 ሰዓት ካሜሩን ከጊኒ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት አልጀሪያ ከአንጎላ ይጫወታሉ፡፡