Fana: At a Speed of Life!

የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲጠናከር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በሚደረገው ርብርብ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ።
“አርብቶ አደርነት የምሥራቅ አፍሪካ ኅብር ቀለም” በሚል መሪ ሐሳብ 19ኛው የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በክልል ደረጃ በጋምቤላ ከተማ በፓናል ውይይት እየተከበረ ይገኛል።
የፓናል ውይይቱ ዋና ዓላማም የክልሉ አርብቶ አደር የእንስሳት ሀብቱን በመጠቀም ሁለንተናዊ ልማትና የልማት ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥ ማስቻል መሆኑን አቶ ኡሞድ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡
 
በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለመፍጠር ፣ በአርብቶ አደሩ ዘንድ የሚስተዋሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ዙሪያ በመወያየት የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የመድረኩ ፋይዳ የጎላ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
 
አርብቶ አደሩን የልማት ተጠቃሚ ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ ሀገራዊ እድገት ማሳካት አይቻልም ያሉት አቶ ኡሞድ÷ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እገዛ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ማስገንዘባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.