አምባሳደሮች ስለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲና ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መከሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባ በ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ ሀገራዊ ንቅናቄ እና በአዲሱ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ላይ ተወያዩ።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የንቅናቄው እና የፖሊሲውን የትኩረት አቅጣጫዎች እና ቁልፍ ስኬቶች አስመልክተው ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ሚኒስትሩ፥ የኢትዮጵያ ታምርት ዘርፈ ብዙ ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ልማት በማፋጠን፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ተወዳዳሪነት በማሳደግ፣ ፈጠራን በማጠናከርና የገቢ ንግድን መተካቱን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም፤ በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች የቴክኖሎጂ ሽግግርና የአቅም ግንባታ መርሐ ግብሮችን በማሳደግ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በማስተዋወቅ፣ የመዳረሻ ገበያ ፍለጋ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ የሚያደርጉትን ጥረት ማሳደግ አለባቸው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች የኢንዱስትሪ ፖሊሲውን እውን ለማድረግ እና ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ ንቅናቄን በተመለከተ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችን አንስተው በፖሊሲና በአፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ልምድና ግንዛቤ ማካፈላቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!