በመዲናዋ የከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በመዲናዋ ከሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት ጋር መክሯል፡፡
በከተማ ደረጃ የተደራጁ 141 ሺህ የሰላም ሰራዊት አባላት መኖራቸውን የቢሮው ኃላፊ ሊዲያ ግርማ በመድረኩ ላይ ገልጸዋል፡፡
እነዚህ የሰላም ሰራዊት አባላት ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት የመዲናዋን ሰላምና ደኅንነት በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የሰላም ሰራዊት አባላቱ በተለይም የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በማድረግ በኩል ሚናቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ይህን ተከትሎ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር ለሰላም ሰራዊቱ አባላት የተግባርና የንድፈ ሃሳብ ትምህርት መሰጠቱን አመላክተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!