Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ከፈንጅ ማምከን ቢሮ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ከፈንጅ ማምከን ቢሮ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገለጸ።

የመከላከያ ፈንጅ ማምከን ቢሮ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ የፀጥታና ደህንነት ትብብር ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የመከላከያ ፈንጅ ማምከን ቢሮ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ታደሰ አመሎ እንደገለጹት፤ ከተመሰረተ ከ20 ዓመት በላይ የሆነው የፈንጅ ማምከን ቢሮ ፈንጅዎችን የማምከንና የማፅዳት ስራ ሃላፊነትን ይዞ እየሰራ ነው።

ቢሮው ከውጪ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ የጋራ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ ከፀጥታና ደህንነት ትብብር ቢሮ የስራ ሃላፊዎች ጋር ዛሬ የልምድ ልውውጥ ማድረጉን ተናግረዋል።

በዚህም በቀጣይ የሙያተኛውን አቅም ለማሳደግ፣ ስልጠና ለመስጠት እና በትጥቅ ለመደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉን ጠቅሰዋል።

በአሜሪካ ኤንባሲ የፀጥታ እና ደህንነት ትብብር ቢሮ ሃላፊ ሻለቃ ናታን ጆልስ በበኩላቸው፤ በፈንጅ ማምከን ቢሮው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መልካም መሆናቸውን እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ተጨማሪ የሚያስፈልጉ ነገሮች ካሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን ያሉት ሃላፊው፤ የልምድ ልውውጡ በጋራ ለመስራት አጋዥ መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.