Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ 1 ሺህ የግል አምራቾችን የሚያግዝ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከጂአይዜድ ጋር በመተባበር አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

የምክር ቤቱን አቅም የሚያሳድግ፣ የአግሪ ቢዝነስ ስራዎች ላይ የአድቮኬሲ እና የፖሊሲ መፍትሄዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ፕሮጀክት ከጂአይዜድ ጋር በመተባበር ይፋ አድርጓል።

ፕሮጀክቱ በተለይም የሽንኩርት፣ አቮካዶ እና አኩሪ አተር ምርታማነትን ማሳደግና የገበያ ሰንሰለትን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በኦሮሚያ፣ አማራ እና ሲዳማ ክልሎች ለሚገኙ 1 ሺህ ገደማ የግል አምራችቾች ዘርፈ ብዙና ተከታታይ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተነስቷል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ኃላፊ መላኩ አዘዘው (ኢ/ር) በዚሁ ጊዜ፥ ፕሮጀክቱ የግሉን ዘርፍ በመደገፍ የግብርና ምርታማነታችንን የሚጨምር ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ለምርቶቻችን የገበያ ሰንሰለቶችን በመዘርጋት የሀገር ውስጥ ገበያው እንዲረጋጋ እና ምርቶቻችን በዓለም ገበያ ተፈላጊነታቸው እንዲጨምር ያደርጋል ብለዋል።

ይፋ የሆነው ፕሮጀክት የምክር ቤቱ ዕቅድ ውጤታማ እንዲሆን እንደሚያግዝ ጠቅሰው፤ ለተግባራዊነቱ እና ለውጤታማነቱ ምክር ቤቱ የበኩሉን ይወጣል ብለዋል፡፡

የጂአይዜድ ተወካይ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ለሚሳ በበኩላቸው፥ ተቋማቸው የግሉን ዘርፍ አቅምና ምርታማነት የሚያሳድጉ የቴክኒክ እና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ የሚያስችለውን ፕሮጀክት ከምክር ቤቱ ጋር በመሆን ይፋ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.