Fana: At a Speed of Life!

የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስጪ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ በተደርገ ማሻሻያ ቀደም ሲል ሲሰጥ ከነበረው የድጎማ መጠን ዝቅ አንዲል መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ የተደረገው በአገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች አና ፐብሊክ ባስ አንዲሁም ሚዲባስ፣ሚኒባስ፣ታክሲዎችና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

በየስድስት ወሩ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች የድጎማ መጠን ማስተካከያ የሚደረግ ሲሆን÷ ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ለቤንዚን ተጠቃሚ አገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች እና ፐብሊክ ባስ ብር 22.36 በሊትር ሲሰጥ የነበረውን ድጎማ ወደ 19.16 በሊትር ዝቅ እንዲል፣ ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲሰጥ የነበረው ብር 23.21 በሊትር ድጎማ በሊትር 19.89 ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

እንዲሁም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ ሚዲባስ፣ሚኒባስ፣ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር የሚሰጠው ድጎማ በየሶስት ወሩ የሚከለስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016ዓ.ም ድረስ ለቤንዚን ተጠቃሚዎች ሲስጥ የነበረው ብር 12.78 በሊትር ድጎማ ወደ 6.39 በሊትር፣ ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲስጥ የበነረው የብር 13.27 ድጎማ ወደ ብር 6.63 በሊትር ተቀናሽ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.