Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለ779 ሺህ ያህል ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት ለ779 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ምገባ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ እንደገለጹት÷ ባለፉት ስድስት ወራት ድጋፍ የሚሹ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ በትምህርት ቤቶች የተለያዩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህ መሰረትም በመዲናዋ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተገቢ ሁኔታ እንዲከታተሉ በቀን ሁለት ጊዜ የምገባ አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

በዚህም 779 ሺህ 231 በላይ ተማሪዎችን የምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ነው ዋና ዳይሬክተሯ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ከምገባ በተጨማሪም የተማሪዎች ዩኒፎርም እና የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት የማሟላት ሥራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

የምገባ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግም ባለሃብቶች እና የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.