ከ20 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የዝቅተኛና መካከለኛ መስመር ቅድመ ጥገና ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ20 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የዝቅተኛና መካከለኛ መስመር ቅድመ ጥገና ሥራ መከናወኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በዚሁ መሠረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ609 ትራንስፎርመሮች የአቅም ማሳደግ ሥራ መከናወኑን ነው ተቋሙ የገለጸው፡፡
በተጨመሪም ከ658 ኪሎ ሜትር በላይ የዝቅተኛ እና ከ786 ኪሎ ሜትር በላይ የመካከለኛ መስመር የመልሶ ግንባታ ሥራ ተከናውኗል ተብሏል፡፡
እንዲሁም ከ20 ሺህ 110 ኪሎ ሜትር በላይ የዝቅተኛና መካከለኛ መስመር እንዲሁም ለ15 ሺህ 209 ትራንስፎርመሮች ቅድመ ጥገና ተደርጓል መባሉን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ቴክኒካልና ቴክኒካል ባልሆኑ ምክንያቶች በተደጋጋሚ እየተስተዋለ ያለውን የኃይል አቅርቦት ችግር ለመቀነስ እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡