የሀገር ውስጥ ዜና

ለከተማ ግብርናና ለችግኝ ተከላ መርሀግብር እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

By Tibebu Kebede

May 31, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለከተማ ግብርናና ለችግኝ ተከላ መርሀግብር እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን በተመለከተ ውይይት ተደረጓል።

በተያዘው አመት በከተማ ደረጃ ለታቀደው 7 ሚሊየን ችግኝ የመትከል እቅድ የመሬት ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የችግኝ ዝግጅቶችም እየተደረጉ ይገኛሉ። የችግኝ ዝግጅቱ በአስተዳደሩና በተደራጁ ወጣቶች የተደረገ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።