Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ከሶማሊላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት እንደሚደግፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውም የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት እንደሚደግፍ አስታውቋል።
የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና ስምምነቱን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ምክር ቤቱ የወጣቶችን ተጠቃሚነት፣ አካታችነት እና ተሳትፎን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት ስምምነቱ ሀገራዊ ጠቀሜታው የጎላ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ፣ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር እና የዲፕሎማሲ አቅምን የሚያሳድግ በመሆኑ ምክር ቤቱ ስምምነቱን ይደግፋል ብለዋል፡፡
አፈፃፀሙም ስኬታማ እንዲሆን የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግረዋል።
ስምምነቱ ለወጣቱ ይበልጥ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ በመሆኑ በሂደቱ የወጣቶችን ተሳትፎም ከፍ በማድረግ እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።
ወጣቶች በስምምነቱ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ለስምምነቱ ትግበራ የበኩላቸውን እንዲወጡ ምክር ቤቱ ይሰራል ተብሏል።
በዘመን በየነ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.