Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ጥምቀት በሰላም እንዲከበር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተራና ጥምቀት በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ለዚህም ከሐይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከማኅበረሰብ ተወካዮችና ከወጣቶች አደረጃጃቶች ጋር ምክክር መደረጉን የመምሪያው የሕዝብ ግንኙነትና የለውጥ ሥራዎች ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ ተናግረዋል፡፡

በሰላም ማስከበር ስራ የሚሠሩ ወጣቶች ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባሕሩ የሚጓዙበትን ጎዳናዎች ከፖሊስና ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚጠብቁ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

ኅብረተሰቡም በዓሉ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር እና በበዓሉ ለሚገኙ እንግዶችም ተገቢውን አቀባበል በማድረግ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.