Fana: At a Speed of Life!

ለተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎችና የተራድዖ ድርጅቶች ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎችና በሰብዓዊ ድጋፍ ተሰማርተው ለሚገኙ የተራድዖ ድርጅቶች ተወካዮች የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ማብራሪያው እና ሪፖርቱ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ነው ተብሏል፡፡

በመድረኩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሃ ሻወል እንዲሁም የመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ ተገኝተዋል።

በመድረኩም አሁናዊ፣ ሀገራዊና ከባቢያዊ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ማብራሪያ እንደተሰጠ ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.