አቶ ደስታ ሌዳሞ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የሚከናወኑ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዩራፕ ዘርፍ ታቅደው እየተገነቡ የሚገኙትን መንገዶች እና የጥገና መንገዶች እንዲሁም የድልድይ ግንባታ ሥራዎችን የስራ አፈፃፀም ገምግመዋል፡፡
በግምገማው ርዕሰ መስተዳደሩ ÷ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
በመሆኑም ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ በመንገዶች ባለስልጣንና በዩራፕ ዘርፍ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መደረጉን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡