የምክር ቤቱን የአሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ለማሻሻል እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሰራር እና የአባላትን የሥነ-ምግባር ደንብ ለማሻሻል እየተሠራ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የምክር ቤቱ የአሰራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ማሻሻያ ሪፖርት ለምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ቀርቧል፡፡
የማሻሻያ ደንቡ የተጀመረውን ሀገራዊ ሪፎርም፣ የምክር ቤቱን አሁናዊ አደረጃጀት እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ለመከተል በሚያስችል መልኩ ትኩረት እንደተደረገ ከቀረበው ሪፖርት ተጠቁሟል፡፡
የምክር ቤቱ የአሰራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 ማሻሻያ ላይ የተሠሩ ሥራዎች ለምክር ቤቱ አስተባባሪ እና አማካሪ ኮሚቴዎች ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበታል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ÷ ደንቡን ለማሻሻል የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮዎችን በመመልከት ከምክር ቤቱ አሁናዊ ሁኔታ ጋር ሊያሰራ የሚችል መሆኑን ለመመልከት ሰፊ ጥናት መደረጉን ጠቁመዋል።
የደንቡ መሻሻል የምክር ቤቱን አሰራር ወጥ እንዲሆን ማስቻልና የታዩ ውስን ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚያስችል ነው ያሉት አፈ-ጉባዔው÷ የደንቡ መነሻና መዳረሻ ህገ መንግስቱ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የምክር ቤቱ አስተባባሪና አማካሪ ኮሚቴዎች ሀሳብ የሰጡ ሲሆን÷ ደንቡ የምክር ቤቱን ገለልተኝነት አስጠብቆ በህግ የተሰጡትን ሃላፊነቶች እንዲወጣ የሚያስችል መሆን ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።
የደንብ ማሻሻያው በምክር ቤቱ ጸድቆ ሥራ ላይ ይውላል ተብሎ እንደሚጠበቅም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!