Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማድረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ደግፌ ደበላ እንዳሉት፥ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ኮሚቴ ተዋቅሮ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል፡፡

ኮሚሽኑ በዓሉ እሴቱን ጠብቆ በድምቀትና በሰላም እንዲከበር ከፌዴራል ፖሊስ፣ አድማ ብተና እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን ጠቁመዋል፡፡

በየአካባቢው ሊፈጠሩ ለሚችሉ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የጸጥታ አካላት ሥምሪት መደረጉንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በበዓሉ አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ወጣቶች ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡

ሕብረተሰቡም ማንኛውንም አጠራጣሪ ጉዳይ ሲመለከት በአቅራቢያ ለሚገኙ የጸጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.