Fana: At a Speed of Life!

የኤመድ ትሬዲንግ ቤተሰብ አባላት 82 ቅርሶችን በስጦታ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤመድ ትሬዲንግ ቤተሰብ አባላት ከአባታቸው በአደራ የተላለፉላቸውን 82 ቅርሶች በታላቁ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬም እንዲቀመጡ በስጦታ አበርክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን በታላቁ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬም እንዲቀመጡ ቅርስ በእጃቸው ያላቸው ዜጎች እንዲያስረክቡ ጥሪ መተላለፉን አስታውሰዋል፡፡

በጥሪው መሰረትም የኤመድ ትሬዲንግ ቤተሰብ አባላት ከአባታቸው በአደራ የተላለፉላቸውን 82 ቅርሶች በዛሬው ዕለት በስጦታ ማስረከባቸውን ተናግረዋል፡፡

ቅርሶቹ በወቅቱ አርበኞች የተገለገሉባቸው ስንቅ መያዣዎች እና ትጥቆች በመሆናቸው በሙዚዬሙ መቀመጣቸው ለበርካታ ጎብኚዎችና ተመራማሪዎች ለዕይታ የሚቀርቡ ይሆናልም ብለዋል፡፡

ቅርሶቹን በክብር ተንከባክበው እዚህ ያደረሱ እና ያስረከቡትን የኤመድ ትሬዲንግ ቤተሰብ አባላትንም በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል፡፡

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ያስቀመጡ ዜጎች ትውልዱ እንዲማርባቸው ለዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬም እንዲያስረክቡም በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.