Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ የሥድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቅቋል።

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ በፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ለቀጣይ ሥራ አቅጣጫዎች ስኬታማነት አቅም መፍጠር የሚችሉ የሥራ መመሪያዎች ተሰጥተዋል፡፡

በሪፖርቶች የተመላክቱ የአፈፃፀም ችግሮች እንዲታረሙ እና በጥንካሬ የተነሱ ነጥቦች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ ምልአተ ሕዝቡን በማሳተፍ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተለያዩ ክልሎች ያሉ እምቅ ሃብቶች በተደራጀ አቅም መውጣት እንዲችሉ ሕዝቡን በማሳተፍ መንቀሳቀስ እንደሚገባው በመድረኩ መገለጹን የፓርቲው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.