Fana: At a Speed of Life!

የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተቸገሩ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝባቸውን የልማት ጥያቄ ለመመለስና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከፍተኛ የሆነ ፈተና እየተጋፈጡና እየተቸገሩ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑካን ቡድናቸው በዑጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያለባቸውን ፈተና በተመለከተ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የባህር በር የሌላት ኢትዮጵያም ችግሩን ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ መሰረት ጥረት እያደረገች እንደሆነ ማስረዳታቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.