አቶ ደመቀ መኮንን ከሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፈይሰል ቢን ፈርሃን አልሳኡድ ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱን ያደረጉት በዳቮስ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጎን ለጎን ሲሆን÷ በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
እንዲሁም በዜጎች አያያዝ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን÷ በጉዳዩ ላይ ሁለቱ ሀገራት በይበልጥ ተቀራርበው መስራት እንደሚገባቸው መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙት ለማጠናከርም በቅርቡ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ለማካሄድ መንግባባት ላይ ደርሰዋል።