የባህር በር ማግኛ እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚያስፈልግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር በር ማግኛ እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚያስፈልግ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን አመለከቱ።
“ያልተቋረጠው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ፣ ጂኦ ፖለቲካዊ እና ከባቢያዊ አተያይ” በሚል ርዕስ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከማህበረሰብ ተወካዮችና ምሁራን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዘውድነህ ቶማስ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ያላት ታሪካዊ ተሳትፎና ዛሬ ላይ የባሕር በር ማግኘት የምትችልበት ሞራላዊና ሕጋዊ አተያይ በምሁራን ውይይት ተደግፎ ሊዳብር ይገባል ብለዋል።
ለዚህም ይህ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱን ጠቅሰው፤ መንግስት የያዘው ዓላማ ተሳክቶ ኢትዮጵያ ሀብቷን አጥታ የቆየችበት ታሪክ ተሽሮ ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ያጣችውን የባህር በር እንድታገኝ የጋራ መግባባት መኖር እንዳለበት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብም ሆነ ከውጭ ለምታስገባቸው ጉዳዮች መንገድ ለመፍጠር የጋራ መግባባት መኖር አለበት ብለዋል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉላ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ ከጥቂት አስርት ዓመታት በፊት በቀይ ባህር አካባቢ አቅም የነበራትና የላቀ ስልጣኔ ባለቤት መሆኗን በቁጭት ሊታወስ ይገባል ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም የባሕር በር ጥያቄው ወቅታዊም ተገቢም እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ለመጣው ሕዝብ ከባህር በር መራቅ ሕልውናውን የሚፈታተን አደጋ እንደሆነ መታወቅ አለበት ይላሉ።
የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳደር አቶ መስፍን ቶማስ በበኩላቸው ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የባህር በር አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በመለሰ ታደለ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!