ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬኒያው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባኤ ጎን ከፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ተገናኝተው በቀጠናዊ እና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።