Fana: At a Speed of Life!

በጃንሜዳ የከተራ በዓል በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የከተራ በዓል የሐይማኖት መሪዎች፣ ምዕመናን እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ከተለያዩ ደብሮች የተነሱ ታቦታትም ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ ጃንሜዳ ደርሰዋል።

በከተራው አከባበር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነማትያስ ተገኝተዋል።

የሰንበት ትምህርት ቤቶችም የተለያዩ ዝማሬዎችን አቅርበዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.