ስፓርት

ኬፕ ቨርዴ ወደ ጥሎ ማለፉ ተቀላቀለች

By ዮሐንስ ደርበው

January 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኬፕ ቨርዴ ወደ ጥሎ ማለፉ የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡

በዛሬው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ሞዛምቢክን 3 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

ጎሎቹንም÷ ቤቤ፣ ያን ሜንዴስ እና ኬቪን ሌኒ አስቆጥረዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ጋናን 2 ለ 1 መርታቷ ይታወሳል፡፡

ኬፕ ቨርዴ በ6 ነጥብ ምድቡን በመምራት ከወዲሁ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን ስታረጋግጥ÷ ግብጽ በ2 ነጥብ በምድቡ የደረጃ ሠንጠረዥ በሁለተኛ ደረጃ ለይ ትገኛለች፡፡

እንዲሁም ጋና እና ሞዛምቢክ በአንድ አንድ ነጥብ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

የዚሁ ምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ÷ ሰኞ ሞዛምቢክ ከ ጋና እንዲሁም ኬፕ ቨርዴ ከ ግብፅ ይገናኛሉ፡፡