Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በ6 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ከ 3 ሺህ 316 ሄክታር መሬት የሚያለማውና በ6 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

የመስኖና የቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት÷ መንግሥት የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር የውሃ ሃብትን በማልማት የአርብቶ አደሩን ሕይወት ለመለወጥ የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ከ14 ሺህ 700 በላይ አባወራዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመው÷ ግንባታውም በሁለት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በበኩላቸው÷ የክልሉ መንግሥት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሐብቶች በአግባቡ በመጠቀም የአርብቶና የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመቀየር በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል።

በዞኑ የተጀመረው ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክትም ከክልሉ ባሻገር እንደ ሀገር በግብርናው ዘርፍ የተገኘውን ውጤት ለማሳደግና ለማስፋፋት እንደሚያስችል አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.