የጥምቀት በዓል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ፡፡
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ጃንሜዳ፣ በጎንደር፣ በላሊበላ እና በተለያዩ አካባቢዎች ተከብሯል፡፡
እንዲሁም በባቱ ደምበል ሐይቅ ደሴቶች እና በምንጃር ሸንኮራ ኢራምቡቲ በድምቀት የተከበረ ሲሆን ፥ በአጠቃላይ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ነው የተከበረው፡፡
ትናንት የጥምቀት ከተራ በዓል በመላ ሀገሪቱ የተከበረ ሲሆን በዚህም በሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት መሰረት ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ ጥምቀት ገብተዋል።
በዛሬው ዕለትም በባህረ ጥምቀት ስፍራ የተለያየ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።