አምባሳደሮች የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበርን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና አምባሳደሮች ልዑካን የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበርን ጎበኙ።
የልዑካን ቡድኑ አባላት የአዕምሮ እና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ግለሰቦችና አረጋውያንን አነጋግረዋል፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን÷ ማዕከሉ እያደረገ ያለውን ሰብዓዊ እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡
አምባሳደሮች እና የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ለማዕከሉ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
አምባሳደሮቹ ለማዕከሉ ስጦታ ያበረከቱ ሲሆን ፥ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ቃል የገቡት።
የማዕከሉ መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ (ዶ/ር) አምባሳደሮቹ ማዕከሉን በመጎብኘት እና ድጋፍ ስላደረጉ ምስጋና ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!