Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ልትጎበኝ የሚገባት ድንቅ ባህልና ታሪክ ያላት ሀገር ናት – የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ልትጎበኝ የሚገባት ድንቅ ባህልና ታሪክ ያላት ሀገር ናት ሲሉ በጥምቀት በዓል የታደሙ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች ተናገሩ፡፡

የጥምቀት በዓልን በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የታደሙ የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች የበዓሉ አከባበር ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ የቅዱስ ማቴዎስ አንግሊካን ቸርች ፓስተር ማርቲን ሬክስ ዊልያምስ÷ በጥምቀት በዓል የሰዎች መሰባሰብ፣ ባህል፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓትና አለባበስ የተለየ ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።

አስደናቂ ባህል፣ ታሪክና የማኅበረሰብ መስተጋብር ለማወቅ ኢትዮጵያ ትክክለኛ የጎብኝዎች መዳረሻ መሆኗን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ የባህል ልብስ አጊጣ የጥምቀት በዓልን የታደመችው ጀርመናዊቷ መሃኪ ግሪስ በበኩሏ÷ የኢትዮጵያውያን ባህል፣ ምግብና አለባበስ እጅግ እንዳስደነቃት ተናግራለች፡፡

ኢትዮጵያ አስገራሚ ባህል፣ ታሪክ፣ አንድነት የሚገኝባት ሀገር መሆኗን በመጥቀስ ቱሪስቶች ቀጣይ መዳረሻቸው እንዲያደርጓት መጠቆሟን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ከእንግሊዝ ለንደን ከተማ የመጡት ሲንዲ ግሎቨር እና ኤሚይ ግሎቨር ኢትዮጵያን ሲጎበኙ የመጀመሪያቸው መሆኑን ጠቅሰው÷ የሕዝቡ አብሮነትና የሃይማኖታዊ ሥርዓቱ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

በቀጣይ ኢትዮጵያን ዳግም የጉብኝታቸው መዳረሻ ለማድረግ መወሰናቸውንም ነው የተናገሩት።

የበዓሉ አከባበር ደማቅና ሰላማዊ እንደነበር የተናገሩት ደግሞ ፈረንሳዊው ሁጎ ፒልክንግቶን ናቸው።

ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን ጨምሮ አስገራሚ ታሪካዊና ባህላዊ ትውፊት ያለባት ሀገር በመሆኗ ጎብኝዎች መዳረሻ ቢያደርጓት የተለየ ልምድ እንደሚኖራቸው አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.