Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጡሎ ወረዳ ደበሶ ከተማ ዛሬ ከሰዓት በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በአደጋው የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በሌሎች አምስት ሰዎች ላይም ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ፋሪድ ይስሐቅ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

“አደጋው የተከሰተውም ከድሬዳዋ ወደ ጭሮ ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ፍሬን አስቸግሮት ፍጥነቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ በመንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችን በመግጨቱ ነው” ብለዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም በጭሮ እና ሂርና ሆስፒታሎች የሕክምና ዕርዳታ እያገኙ ነው ብለዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.