ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ የኦዲዮን ኢጋሎን ኮንትራት አራዘመ

By Tibebu Kebede

June 01, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ የናይጀሪያዊውን አጥቂ ኦዲዮን ኢጋሎን ኮንትራት ለተጨማሪ ወራት ማራዘሙን አስታወቀ።

ክለቡ አጥቂውን እስከ መጭው ጥር ወር ድረስ ለማቆየት መስማማቱን ነው ያስታወቀው።

የናይጀሪያዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ቆይታ ትናንት አብቅቶ ነበር።

የክለቡ አሰልጣኝ ኦሊጉናር ሶልሻዬር የቻይናው ክለብ ለተጫዋቹ ለፈጠረለት ተጨማሪ እድል ምስጋና አቅርበዋል።

ባለፈው ጥር ወር ማንቼስተርን የተቀላቀለው ኢጋሎ በ8 ጨዋታዎች 4 ጎል ማስቆጠር ችሏል።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ 10 ቀን ይጀመራል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ