Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ሥራ ይጠበቃል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እና የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማስተካከል የላቀ ዲፕሎማሲ አፈፃፃም እንደሚጠበቅ አመላከቱ፡፡

አቶ ደመቀ በዓመታዊው የሚሲዮን መሪዎች ስብሰባ ላይ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸውም በያዝነው የበጀት ዓመት ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር፣ ወዳጅ ለማብዛት፣ የተደናገረውን ለማቅረብ፣ የላቀ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ በአጽንኦት አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ÷ በአብሮነት፣ ዘላቂና የጋራ ልማት እንዲሁም ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከሁሉም ሀገሮች ጋር ተደጋግፋ እንደምትሠራም አረጋግጠዋል፡፡

ለዚህም በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ፣ አኅጉራዊ እንዲሁም የባለ-ብዙ ወገን የዲፕሎማሲ መስኮች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በስዊዘርላንድ ዳቮስ ሲካሄድ በቆየው የዓለም አቀፉ የምጣኔ-ሐብት ጉባዔ ሲሳተፉ የቆዩት አቶ ደመቀ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.