Fana: At a Speed of Life!

8ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል ከጥር 16 ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምንተኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል ከፊታችን ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አስፋው ኩማ÷ ፌስቲቫሉ ከጥር 16 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በአዲስ አበባ ሙዚዬም እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በተዘጋጀው የንባብ ባህል ፌስቲቫል በከተማው ለንባብ ባህል ዕድገት የሚያግዙ መልዕክቶች በማዘጋጀት ተደራሽ እንደተደረገ ገልጸዋል።

በዚህም አዲሱ ትውልድ ጊዜውን አልባሌ ቦታ እና በማይጠቅሙ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ተጠምዶ ከማሳለፍ እንዲቆጠብና ንባብን ባህል እንዲያደረግ ለማነቃቃት አበርክቶ ማድረጉን ተናግረዋል።

ዘንድሮም ስምንተኛው ዙር ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል ”አንባቢ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በፌስቲቫሉ በህትመት ዘርፍ ዕድሜ ጠገብ የሆኑ ማተሚያ ቤቶች፣ ደራሲያን፣ በመጻሕፍት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ አካላት እን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.