ኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ከፍ እንዲል የአመራር ብቃት ወሳኝ ነው – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ለማድረግ ሁለንተናዊ የአመራር ብቃት የማይተካ ሚና አለው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ አስገንዝበዋል።
ሁለንተናዊ የአመራር ሥነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ሥልጠና በምክር ቤቱ እየተሠጠ ነው።
በስልጠና መድረኩ ላይ አፈ ጉባዔው እንዳሉት፤ የምክር ቤቱ አመራሮችን አቅም በመገንባት የህዝብን አደራ በብቃት እንዲወጡና ሀገርን ከፍ የሚያደርጉ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ማድረግ ይጠበቃል።
ስልጠናውን የሰጡት ታሪኩ ፉፋ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ለማድረግ እና የህዝቡን ግንዛቤ ለማጎልበት የአመራር ብቃትን ማሳደግ ድርሻው የጎላ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በውስጡ ዕውነታን የተላበሰ አመራር ለማፍራት ያስችል ዘንድ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ተሞክሮዎችን በማጣቀስ የአመራር ብቃት ለአንድ ሀገር ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አስረድተዋል፡፡
ምክር ቤቱ ህግ አውጭ እንደመሆኑ መጠን በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ሁለንተናዊ የሥነ-ምግባር አመራር ዘዴን መተግበር አጋዥ እንደሚሆን አሰልጣኙ ጠቁመዋል፡፡
በሀገሩ አመራር እና ተቋማት የሚኮራ እና በራሱ የሚተማመን ዜጋን ለማፍራት የሁሉም አካላት ተሳትፎ በተግባር መገለጥ እንዳለበት ታሪኩ ፉፋ (ዶ/ር) መናገራቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!