ስፓርት

አትሌት ለሜቻ ግርማ በፈረንሳይ ሌቪን በሚካሄደው የ3 ሺህ ሜትር ውድድር ይሳተፋል

By Mikias Ayele

January 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ክብረ ወሰን ባለቤት ለሜቻ ግርማ በፈረንሳይ ሌቪን በሚካሄደው የ3 ሺህ ሜትር ውድድር እንደሚሳተፍ ተገለፀ፡፡

አትሌቱ ባለፈው የውድድር ዘመን በፈረንሳይ ሌቪን በ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር በ7 ደቂቃ 23 ሰከንድ 81 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሪከርድ ማሻሻሉ የሚታወስ ነው፡፡

ክብረወሰኑ ለ25 ዓመታት በኬንያዊው አትሌት ዳንኤል ኮመን ተይዞ መቆየቱም አይዘነጋም፡፡

የፈረንሳይ ሌቪን የቤት ወስጥ ውድድር የካቲት 10 የሚደረግ ሲሆን አትሌት ለሜቻ ከዚህ ወድድር ቀደም ብሎ በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጥር 18 እንደሚሳተፍም ተመላክቷል፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን