Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሰመሪታ ከኖርዌይና ስዊድን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው ከኖርዌይ እና ስዊድን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወ/ሮ ሰመሪታ÷በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም የሰብዓዊ እና የሰላም ግንባታ ሥራዎች አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ እና የትብብር ታሪክ ያላቸው ሁለቱ ሀገራት በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራ የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተሮች በበኩላቸው÷ለሀገር ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለሚያደርገው የግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ለዚህም ሀገራቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን የገንዘብሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.