Fana: At a Speed of Life!

“ዓድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)”ዓድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

ሰላም ሚኒስቴር ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ሀገራዊ የምክክር መድረክ “ዓድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ሀገራዊ እሴቶች” በሚል መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።

በመድረኩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ( ዶ/ር) ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መሐመድ ዑስማን(ዶ/ር)፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ ምሁራን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የምክክር መድረኩ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰላምና ሀገር ግንባታ ፎረም እስከ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ‹‹ዓድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ›› በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ አካል መሆኑም ተገልጿል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.