ኢቲዮ ቴሌኮም 11 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢቲዮ ቴሌኮም ባለፉት ሥድስት ወራት 11 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።
የኢቲዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የኩባንያውን የሥድስት ወራት ስራ አፈፃፀም በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ በአጠቃላይ 42 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
84 ነጥብ 7ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱንም ነው የገለጹት፡፡
የደንበኞች ቁጥርም 74 ነጥብ 6 ሚሊየን መድረሱን ተናግረዋል፡፡
የቴሌ ብር ተጠቃሚዎች ደግሞ 41 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱንም ነው የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፡፡
1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር በቴሌ ብር መንቀሳቀሱንም አስታውቀዋል፡፡
በትዕግስት ስለሺ እና ይስማው አደራው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!