የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የ2016 ምርት ዘመን ስኳር የማምረት ሥራውን የሸንኮራ አገዳ በመፍጨት ጀምሯል፡፡
በዚህ ዓመት በ4 ሺህ 600 ነጥብ 5 ሄክታር ላይ የለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠቀም 245 ሺህ 927 ነጥብ 5 ኩንታል ስኳር ለማምረት አቅዶ ወደ ሥራ መግባቱም ተገልጿል፡፡
የፋብሪካው አጠቃላይ የክረምት ጥገና ተከናውኖ ታኅሣስ 26 ቀን 2016ዓ.ም ቦይለር መለኮሱን ከኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡