በኦሮሚያ ክልል 5 ሺህ 369 የመምህራን መኖሪያ ቤቶች ተገነቡ
በቢሮው የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን እድሪስ እንዳሉት፥ በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በዚህም ለመማር ማስተማር ሒደቱ እና ለትምህርት ጥራት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በጥናት የመለየት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም የመማር ማስተማር ሒደቱ የጀርባ አጥንት ለሆኑት መምህራን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ተሰርቷል ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራትም ከ4 ሺህ 500 በላይ የመምህራን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ 5 ሺህ 369 ቤቶችን በመገንባት ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡
በቀጣይ ለመምህራን ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እና በትምህርት ጥራት ላይ የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ