ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ትምህርት ቤቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ሥድሥት ትምህርት ቤቶች ተመረቁ፡፡
የተመረቁት ትምህርት ቤቶችም አምሥት የመጀመሪያ ደረጃ እና አንድ ሁለተኛ ደረጃ ሲሆኑ÷ የግንባታው ወጪም በፌዴራል፣ ክልል እና በከተማ አሥተዳደሩ መሸፈኑ ተገልጿል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወንደሰን ልሳነወርቅ በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የተገነቡት የትምህርት ተቋማት ሞዴሎቻችን ናቸው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ማሕበረሰቡን በማሳተፍ ግብዓት የማሟላት ሥራ እንደሚከናወን አመላክተዋል፡፡
የከተማ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ መንግሥቱ አበበ በበኩላቸው÷ የትምህርት ተቋማቱ ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙ የተማሪ ወላጆችም መንግሥት ባደረገው ሁለንተናዊ ትብብር ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች ተገንብተውልናል፤ በቀጣይም ግብዓት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ እናበረክታለን ብለዋል፡፡
በእሸቱ ወ/ሚካኤል
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!