ከሀገር ውስጥ ታክስ 168 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ከሀገር ውስጥ ታክስ 168 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ተስፋዬ ቱሉ እንዳሉት÷በግማሽ ዓመቱ ከሀገር ውስጥ ታክስ 167 ነጥብ 44 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 168 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡
በዚህም የዕቅዱን 100 ነጥብ 50 በመቶ ማሳካት መቻሉን ጠቁመው÷ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ29 ነጥብ 46 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው አንስተዋል፡፡
የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው አንጻር በታክስ አሰባሰቡ ላይ ውስንነቶች መኖራቸውን እንደገለጹም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!