Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድና ኢንዱስትሪ ም/ቤት የ2024 ሽልማትን አሸነፈ

አዲሰ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ በሚከናወነው የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “Corporate Sustainability Achievement Award” አሸናፊ ሆነ።

ሽልማቱ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ለሚኖረው የንግድ ትስስር፣ የአፈፃፀም ልህቀት እና ፈጠራ ዕውቅና የሚሰጥ እንደሆነ ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የብሪክስ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በአባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ የንግድና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎችን ለማበረታታት በፈረንጆቹ 2012 የተቋቋመ ምክር ቤት ነው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.