Fana: At a Speed of Life!

በብሄራዊ ቴአትር የቻይና የባህል ፌስቲቫልና ትርኢት እየተካሄደ ነው

አዲሰ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 የቻይና አዲስ አመትን አስመልክቶ በብሄራዊ ቴአትር የቻይና የባህል ፌስቲቫልና ትርኢት እየተካሄደ ነው።

የቻይና አፍሪካን ወዳጅነት ያጠናክራል የተባለው ፈስቲቫል÷በመጪው የካቲት 2 ቀን 2016ዓ.ም የሚከበረውን የቻይናውያን አዲስ አመት አስመልክቶ እንደተዘጋጀም ተገልጿል፡፡

የቀደመ ስልጣኔ ባለቤት የሆኑት ቻይና እና ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ በባህል፣ በንግድ፣ በትምህርትና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ወዳጅነት እንዳላቸው ይታወቃል።

በዚህም የባህል ፌስቲቫሉ የሁለቱን ሀገራት የባህል ልውውጥ የሚያሳድግና ሀገራቱ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነ ነው የተገለጸው።

በፌስቲቫሉ ስፓርታዊ ትርኢቶችን ጨምሮ ሌሎች ትዕይንቶች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

በትዕግስት ብርሃኔ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.