Fana: At a Speed of Life!

የሻይ ቅጠልን በ30 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ ነው-አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በዚህ አመት 490 ሚሊየን የሻይ ችግኞችን በማዘጋጀት 30 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡

ርእሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”በግብርናው ዘርፍ ከያዝናቸው ግቦች መካከል አንዱ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርትቶችን አይነትና ብዛት ማሳደግ ነው”ብለዋል።

ይህንን ግብ በማሳካት ረገድ የምዕራብ ክላስተር የሻይ ቅጠል ልማት ኢኒሼቲቭ እንቅስቃሴ ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

የሻይ ቅጠል ምርትን በብዙ እጥፍ ለመጨመር በተያዘው እቅድ መሠረት በዚህ አመት 490 ሚሊየን የሻይ ችግኞችን በማዘጋጀት 30 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

” የግብርና ባለሙያዎቻችን ጥንካሬ፣ የአርሶ አደሮቻችንና የመላው ወጣቶቻችን ተሳትፎ ተጠናክሮ ከቀጠለ ተጨማሪ የሻይ ልማት መሬት በመለየት ከእቅድ በላይ መሳካት እንደሚቻል የመጣንበት መንገድ ያሳያል” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

የተጀመረው የመንግሥት ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.