Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄድ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው በስብሰባውም ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ተመላክቷል፡፡

ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸው ይዘቶች በመርሐ ግብሩ ላይ በአግባቡ እንደሚመከርባቸው የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም እንደ ሀገር በብሔራዊነት ትርክት የተጀመረው ጉዞ ማጠናከር የሚችሉ ግብዓቶች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ውይይቱ በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን÷ ገለጻዎች እና የቡድን ውይይቶች የመርሐ ግብሩ አካል ናቸው ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.