Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን አጀንዳ የሚሰጡ ተወካዮችን መረጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን አጀንዳ የሚሰጡ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮችን መርጧል።

በየም ዞን ሳጃ ከተማ በተካሄደው አጀንዳ የሚሰጡ ተወካዮች መረጣ መድረክ ላይ ከ325 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የፖለቲካ እና የሃሳብ መሪዎች መካከል እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልዩነትና አለመግባባት ይታያል፡፡

ይህን ልዩነት እና አለመግባባት ለመፍታትም ሰፋፊ ሀገራዊ የሕዝብ ምክክሮች አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር አስፋላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመድረኩ እንደ ሀገር እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች መንስኤና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

በየም ዞን የሚገኙ ከ3 ወረዳዎችና ከአንድ ከተማ አስተዳደር ከእያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል ሁለት ሁለት ተወካዮች እና አንድ አንድ ተጠባባቂም ተመርጧል።

በተስፋሁን ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.