Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
 
አደጋው መነሻውን ደሴ አድርጎ ወደ አቀስታ ሲጓዝ በነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ ነው የደረሰው፡፡
ሚኒባሱ 21 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን÷ከእነዚህ ውስጥም የ13ቱ ሰዎች ሕይወት ማለፉን በደሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የትራፊክ ባለሙያ ዋና ሳጅን ኤፍሬም ይመር ተናግረዋል፡፡
 
በተጨማሪም በአደጋው 7 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
 
ባለሙያው የአደጋው መንስዔ እየተጣራ እንደሆነ መናገራቸውንም የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.